top of page

በጤና ህግ (Health Law) ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ሊጀመር ነው

Writer's picture: Melkamu MeazaMelkamu Meaza

University of Gondar [UOG] has announced that it will offer postgraduate program leading to master's degree in Medical Law, the first of its kind in Ethiopia.


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት የ2014ዓ/ም የስራ ዘመን የስራ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2015 ዓ/ምን የስራ እቅድ ትውውቅና በኽልዝ ሎው ስርዓተ ትምህርት (Health Law curriculum) ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሀምሌ 29/2014ዓ/ም በፍሎሪዳ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡


በመርሃ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ልጃለም ጋሻው፣ የህግ ትምህርት ቤት ዲን አቶ አለሙ ታዬ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተምረው በህግ መምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በአሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሀገር በሲያትል ዋሽንግተን ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ እዮብ ከበደና ሌሎች የትምህርት ቤቱ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፣ በቅድሚያ አቶ እዮብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የጤና ህግ (Health Law curriculum) ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲው በ2ኛ ዲግሪ ለመክፈትና ከዩኒቨርሲቲው ጋር ለመስራት ያላቸውን ፈቃደኝነትንና ተነሳሽነት በዩኒቨርሲቲው፣ በራሳቸውና በህግ ትምህርት ቤቱ ስም አመስግነዋል፡፡ ዶ/ር ካሳሁን አያይዘውም ፕሮግራሙ በዩኒቨርሲቲው መሰጠቱ የሚኖረውን ፋይዳና ተያያዥ ነጥቦችን በማንሳት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው፣ በሚቀርበው የስራ ሪፖርትና እቅድ ላይ ተሳታፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል፡፡


በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኽልዝ ሎው (Health Law curriculum) ፕሮግራምን በ2ኛ ዲግሪ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚያነሱት አቶ እዮብ የፕሮግራሙን አስፈላጊነት አስመልክቶ፣ፕሮግራሙ ለዩኒቨርሲቲውና እንደ ሀገርም ያለውን ፋይዳ፣ በአጠቃላይ የፕሮግራሙን ጠቀሜታ እንዲሁም ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ አጭር ገለፃ አድርገዋል፡፡ ገለፃውን ተከትሎ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመቀጠል የህግ ትምህርት ቤት ዲን በሆኑት በአቶ አለሙ ታዬ የ2014ዓ/ም የስራ ዘመን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ እቅድ በመነሳት የህግ ትምህርት ቤቱ የ2015 ዓ/ም የስራ እቅድ መታቀዱንና በሚቀጥለው የስራ ዘመን ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወኑ ተግባራትንም አቶ አለሙ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡


በመጨረሻም በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

********************

ለልህቀት እንተጋለን!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ሀምሌ 29/2014ዓ.ም




K

28 views0 comments

Recent Posts

See All

Comentarios


CONTACT US >

       +251 91  198 3005 / +251 93  496 4318

          kutolalae@gmail.com

MECE Transparent 2.png

CONNECT WITH US >

  • Facebook
  • telegram
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube

©2025 Medicolegal & Ethics Consulting - Ethiopia [MECE]. All Rights Reserved.
 

bottom of page